Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና ትብብር ሚኒስትር ፍራንሲስኮ አንድሬ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅምና ወሳኝ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ ከፖርቹጋል ጋር ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ትብብር እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ ሁለተኛው የጋራ የፖለቲካ ምክክር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሁለቱም ወገኖች በፖለቲካዊ ትብብር፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ ትምሕርት፣ አኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጥቅሞች ላይ በማተኮር በትብብር መሥራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በተመሳሳይ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከካናዳ አምባሳደር ጆሹዋ ታባን ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.