Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል አንድ የሃማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በፈጸመችው የአየር ላይ ጥቃት አንድ የሃማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መግደሏን አስታውቃለች፡፡

ኢብራሂም ቢአሪ የተባለው የሃማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የእስራኤል ጦር በጋዛ ሠርጥ አካባቢ በፈጸመው የአየር ላይ ጥቃት ነው የተገደለው፡፡

ወታደራዊ አዛዡ በሳለፍነው ጥቅምት 7 ቀን ሃማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ካቀናበሩት ውስጥ አንዱ መሆኑን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የእስራኤል እግረኛ ጦር በቀጣናው ባካሄደው ዘመቻም ሃማስ ሲገለገልባቸው የነበሩ ይዞታዎችና መሰረተ ልማቶችን መቆጣጠር መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

በአንጻሩ የእስራኤል ጦር በጋዛ ሠርጥ አካባቢ ባካሄደው የአየር ላይ ጥቃት ንጹሃን ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተመላክቷል፡፡

ይህንን ተከትሎም ሳዑዲ ዓረቢያና ቦሊቪያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ድርጊቱን እየኮነኑት እንደሚገኙ ሬውተርሰ በዘገባው አስፍሯል፡፡

በእስራኤል እና ሃማስ መካከል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት እስካሁን በጋዛ ከ8 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.