Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ እና መቻል ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 5ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

9 ሰአት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ አዳማ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የአዳማ ከተማን ግቦች አብዲሳ ጀማል እና አሰጋኸኝ ጴጥሮስ (በራሱ ላይ) ሲያስቆጥሩ ዘርዓይ ገብረስላሴ ደግሞ የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተክትሎ አዳማ በ11 ነጥብ ለጊዜው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በፕሪሚየር ሊጉ ደካማ አጀማመር ያሳየው ድሬዳዋ ከተማ 4 ነጥቦችን ይዞ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

እንዲሁም 12 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ መቻል ሀምበሪቾ ዱራሜን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የመቻልን ብቸኛ ጎል ያሬድ ከበደ ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን÷ መቻል በውድድር ዓመቱ የሰበሰባቸውን ነጥቦች 10  በማድረስ ደረጃውን ወደ ሦስት ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.