Fana: At a Speed of Life!

የኮሮናቫይረስ በአንድም የሀገሪቱ ማረሚያ ቤት በሚገኝ ታራሚ ላይ አለመገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ በአንድም የሀገሪቱ ማረሚያ ቤት በሚገኝ ታራሚ ላይ አለመገኘቱን የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጠው፥ ኮቪድ-19 በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኝ በአንድ በፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና ጉዳያቸውን በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንኪኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት 66 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብሏል።

ከዚህ ውጭ “በማረሚያ ቤት በሚገኙ የህግ ታራሚዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል” በሚል የተናሰፈው ምረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ3 ሺህ 460 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተኘባቸው ሲሆን፥ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 389 ደርሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.