Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ እየወሠደ ባለው የተጠናከረ እርምጃ ሠላም ማረጋገጥ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠራዊቱ እየወሠደ ባለው የተጠናከረ እርምጃ በተለያዩ ዞኖች ሠላም ማረጋገጥ መቻሉ ተገለጸ፡፡

በተለያዩ ዞኖች በኅቡዕ ተደራጅተው በመንግሥታዊና ሕዝባዊ ተቋማት ላይ ውድመትና ዝርፊያ በነዋሪው ላይ ግድያና እገታ ሲፈፅሙ በነበሩ አክራሪ ኃይሎች ላይ ባለፉት ጥቂት ወራት በተወሰደ እርምጃ መደምሰሳቸውን የዕዙ አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ተናግረዋል።

ዕዙ በቀጣናው ከሚገኙ ከዞን አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣ ከፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ከዕዙ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

ከዚህ ቀደም እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው በርካታ በደሎች በሕዝብ ላይ መፈጸማቸው በውይይቱ ላይ ተብራርቷል፡፡

ሆኖም ጽንፈኛ ኃይሎቹ በሠራዊቱና በአካባቢው የፀጥታ ኃይል የተቀናጀ ስምሪት አከርካሪያቸው ተመትቶ ስጋት ወደ ማይሆኑበት ደረጃ ደርሰዋል መባሉን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት አሁን በቀጣናው የሚገኘው የሸኔም ይሁን የፅንፈኛው ቡድን ከፀጥታ ኃይሎቻችን አቅም በላይ አይደሉም ብለዋል።

ዋናው ችግር የቁርጠኝነትና በውስጥ ተመሳስሎ የሚጓዝን ጠላት ለይቶ እርምጃ ያለመውሰድ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በቀጣይ እነዚህን የውስጥ የሕዝብ ጠላቶች በመለየት ርምጃ እየወሰድን የጠላቶቻችንን የገቢ ምንጭ በማድረቅ አስተማማኝ ፀጥታ ለማስፈን እንሠራለን ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.