Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የደቡብ ኮሪያ የባህል ልውውጥ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ የባህል ልውውጥ ሥነ- ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የቾንቹን ከተማ ከንቲባ ዮክ ዶንግ ሃን እና ልዑካን ቡድናቸው፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የቃኘው ሻለቃ የኮሪያ ዘማቾች ተገኝተዋል፡፡

መርሐ ግብሩ የአዲስአበባ እና የቾንቹን ከተሞችን 20ኛ ዓመት የእህትማማችነት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ እንደተዘጋጀ የከተማ አስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያና የደቡብ ኮሪያ ወዳጅነት ታሪካዊ ግንኙነትን ወደሚመጥን ተጨባጭ ሥራ በመቀየር የባሕል ትስስር የሚያጠናክር ዝግጅት ማምሻውን መካሄዱን ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡

በምሽቱ መርሐ- ግብርም በሁለቱ ከተማ ወጣቶች ወዳጅነትን የሚያጠናክሩ ጨዋታዎች መቅረባቸውን ነው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡

የቾንቹን ከንቲባ ለኮሪያ ቃኘው ዘማቾች እና ቤተሰቦች ስጦታ ማበርከታቸውንም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.