Fana: At a Speed of Life!

500 ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃና አካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በኢትዮጵያ 500 ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃና አካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡

በኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው ፕሮጀክቱ÷ 500 ሺህ ኢትዮጵያውያንን የውሃ አቅርቦት አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

በዚህም 120 የውሃ፣ ሳኒቴሽንና ንጽህና ላይ የሚሠሩ ተቋማት ማጠናከር በፕሮጀክቱ ትግበራ ከተያዙ ግቦች መካከል መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር አስፋው ዴንጋሞ÷ በኢትዮጵያ የውሃና ንጽህና አገልግሎቶችን ለማሣለጥ መንግሥት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በተከናወኑ ሥራዎች የተመዘገበ ውጤት ቢኖርም አሁንም ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል።

ዛሬ ይፋ የሆነው ፕሮጀክት ለዜጎች ተጠቃሚነት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው÷ ሰዎችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራት ላይ በመሳተፋችን የላቀ ኩራት ይሰማናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ፕሮጀክትም የሀገራቱን በጋራ የመሥራትና የትብብር ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.