Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ሥራዎች ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2016 ዓ.ም የግብርና ተግባራት ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በዲላ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ÷ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዓለማየሁ ባውዲን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ እና የሰው ኃይል በማቀናጀት የሚከናወኑ ሥራዎች ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰረት መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኃይለ ማርያም ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ቢሮው ሕዝቡን ከድህነት ለማላቀቅ በአዲስ እሳቤ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንሻገር በሚል መሪ ሐሳብ በቁርጠኝነት ይሠራል ብለዋል፡፡

በጥላሁን ሁሴን

በጥላሁን ሁሴን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.