Fana: At a Speed of Life!

ከ6ኛ እስከ 15ኛ ሣምንት በሚካሄዱ የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ- ግብሮች ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ6ኛ እስከ 15ኛ ሣምንት ባለው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ- ግብር ላይ የቀናት ማሻሻያ መደረጉን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ።

በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚደረገው የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የ5ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ከተካሄደ በኋላ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት ለጊዜው እንደሚቋረጥ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ከ6ኛ ሣምንት በኋላ የሚደረጉ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች የብሔራዊ ቡድኑን እና የኢትዮጵያ ዋንጫ መርሐ- ግብርን ታሣቢ በማድረግ የቀናት ማሻሻያ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.