Fana: At a Speed of Life!

የቼክ ሪፐብሊክ ጠ/ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለፁ፡፡

ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ ለበርካታ ዘመናት በወታደራዊ ትብብር እና በኢኮኖሚ ዘርፎች የቆየ ግንኙነት እንዳላቸው አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ያደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝትም እነዚህን ታሪካዊ ግንኙነቶች እና ትብብሮች የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በነበራቸው ውይይትም÷ በኢኮኖሚ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ያሉ ዕድሎችን በተመለከተ መክረዋል ብለዋል፡፡

በተለይም በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በወታደራዊ ቴክኖሎጂ ትብብር እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውንም አስረድተዋል፡፡

የመሪዎቹ ውይይቱ ውጤታማ እንደነበር አስታውሰው÷ ውይይቱ ሀገራቱ በይበልጥ ተቀራርበው መሥራት እንዲችሉ እና ያሉ የትብብር ማዕቀፎችን ማስፋት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.