Fana: At a Speed of Life!

የተሳካ የሀገረ መንግስት ግንባታ እንዲኖር ዜጎችን ወደ አንድ የሚያሰባስብ ትልቅ ትርክት ያስፈልጋል – አቶ ተስፋዬ በልጅጌ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተሳካ የሀገረ መንግስት ግንባታ እንዲኖር ዜጎች ወደ አንድየ የሚያመጣና የሚያሰባስብ ትልቅ ትርክት ያስፈልጋል ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌገለጹ።

የሰሞኑ ትልቅ ርዕሰ ጉዳይ በሆነው ‘ታላቁ ትርክት’ ዙሪያ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ እንደገለጹት÷የተዛባ ትርክትን ማረም ሀገርን ከችግር ያወጣል።

የተሳካ የሀገረ መንግስት ግንባታ እንዲኖር ቁልፍ መሳሪያ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ አሰባሳቢና ሁሉም የሀገሩ ዜጎች ወደ አንድ እንዲመጡ የሚያስችል ትርክት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ስለዚህ የሀገረ መንግስት ግንባታ የተቃና እንዲሆን የሚያግባባ ትርክት መኖር እንዳለበት ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ሁለት ጽንፍ የወጡ ትርክቶች እንደነበሩ አስታውሰው÷በነዚህ የተራራቁ ትርክቶች የተነሳ ሀገሪቱ ለችግር ተዳርጋ መቆየቷን ገልጸዋል።

በመሆኑም ዜጎችን ወደ አንድ የሚያሰባስብ የጋራ የሆነ ታላቅ ትርክት አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

ታላቁ ትርክት ሁላችንም በአንድነት ሊያሰባስበን የሚችል ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ÷ታላቁ ትርክት ህብረ ብሔራዊነትን፣ አካታችነትን፣ እኩልነትን፣ ፍትሐዊነትን እንደያዘ አብራርተዋል።

ለታላቁ ትርክት አጀንዳ ሆኖ መምጣት ዋናው ምክንያት የተዛቡ ትርክቶች መኖራቸው እንደሆነ ጠቅሰው÷ እነዚህ የተዛቡ ትርክቶች አሁን ለሚታዩ ችግሮች መንስኤ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች በተለይም በፖለቲካ ባህል ውስጥ ያለው በሽታ መነሻው የተዛባ ትርክት በመሆኑ ትርክቱን ማስተካከል እንደሚገባ ታምኖበታል ብለዋል።

የተሳሳተ ትርክትን ለማረም ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ እንደነበር አስታውሰው÷አሁን በተጨባጭ ወደ ተግባር እየተገባ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ቁልፍ ችግሮች ከሆኑት መካከል አንዱ የትርክት ችግር መሆኑን በግምገማና በጥናት መለየቱን ገልጸው÷እንደ መሪ ፓርቲ ብልጽግና ይህንን ችግር ለመፍታት መፍትሄ የማመንጨትና ለውይይት የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት አመልክተዋል።

በዚህ ረገድ ህብረ ብሔራዊነትን፣ አካታችነትን፣ እኩልነትን፣ ፍትሐዊነትን የያዘ አሰባሳቢ የሆነ ታላቅ ትርክት እውን እንዲሆን ሁሉም ዜጎች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.