Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ታምራት ቶላ የዘንድሮውን የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ታምራት ቶላ የዘንድሮውን የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር በአሸናፊነት አጠናቀቀ።

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዘንድሮውን የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች።

በውድድሩ በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ 2:04:58 በሆነ ሰዓት በመግባት በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፤ ኬኒያዊው አትሌት አልበርት ኮሪሪ 2:06:57 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ወጥቷል።

ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሹራ ቂጣታ 2:07:11 በሆነ ሰዓት በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በሴቶች ደግሞ ኬኒያዊቷ አትሌት ሄለን ኢቢሪ 2:27:23 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ስታሸንፍ፤ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ 2:27:29 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ከሶስተኛ እስከ ሰባተኛ ድረስ ያለውን ደረጃ በመያዝ ኬኒያውያን አትሌቶች ውድድሩን አጠናቀዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.