Fana: At a Speed of Life!

‘ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለድህረ ግጭት ለውጥ በኢትዮጵያ’ በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለድህረ ግጭት ለውጥ በኢትዮጵያ’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ውይይቱ በዋናነት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጦርነት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሠላም፣ እርቅና ማህበራዊ ትስስርን እንዴት ማስፈን እንደሚችሉ ግንዛቤ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ÷ የአካባቢውን ማህበረሰብ ልማት ለመደገፍና እውቀታቸውን ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉበትን መንገድ ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ውይይቱን ወሎ፣ መቀሌና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች ከአሜሪካ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር አዘጋጅተውታል።

በውይይቱ ላይ የትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች አመራሮች፣ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሶስቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ዲፕሎማቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.