Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጄ አይ ቢ ኤች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጃፓን የኢንዱስትሪና የቤት ግንባታ ዓለም አቀፍ ማህበር (JIBH) ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ኩኒሂሮ ሃሺሞቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማ በኢትዮጵያ እያደገ ለመጣው ኢኮኖሚና የቤት ፍላጎት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ለኢትዮጵያ አስፈላጊ የሆኑ የጃፓን የዘርፉ ቴክኖሎጂዎችንና ልምድ  ማሸጋገር ስለሚቻልበት ሁኔታ የሃሳብ ልውውጥ ማድረግ ነው ተብሏል።

በዚህም መነሻ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷በቀጣይ ከኢትዮጵያና ከጃፓን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ተከታታይ ውይይትና ጉብኝት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በውይይቱ የጃፓን የኢንዱስትሪና የቤት ግንባታ ዓለም አቀፍ ማህበር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም መገኘታቸውን በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.