Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት በኒው ዮርክ ማራቶን አፍሪካን ላስጠሩ አትሌቶች ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ጽ/ቤት በኒው ዮርክ ማራቶን የአፍሪካን አህጉር ላስጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን አትሌቶች ምስጋና አቅርቧል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ ÷በኒው ዮርክ ማራቶን ላሸነፉ የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሰረት በኒው ዮርክ ማራቶን ላሸነፈው ኢትዮጵያዊ አትሌት ታምራት ቶላ ፣ 3ኛ ለወጣው አትሌት ሹራ ቂጣታ እንዲሁም 2ኛ ሆኖ ላጠናቀቀው ኬንያዊ አትሌት አልበርት ኮሪር እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ 2ኛ ደረጃን ይዛ ላጠናቀቀችው ኢትዮጵያዊ አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና 1ኛ እና 3ኛ ለወጡት ኬንያውያን አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ እና ሻሮን ሎክዲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

አትሌቶቹ በተካሄዱት ውድድሮች የአፍሪካን ስም በማስጠራት ላስገኙት ኩራትም ህብረቱ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.