Fana: At a Speed of Life!

የዋልያዎቹ ሁለት ተጫዋቾች ከስብስቡ ውጭ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ትናንት ዝግጅት መጀመሩ ይታወሳል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር።

ጌታነህ ከበደ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ ከስብስቡ ውጭ መሆኑ ሲረጋገጥ ሌሎቹ ሁለት ተጫዋቾችም ከቡድኑ ስብስብ ውጭ መሆናቸው ታውቋል።

በዚህም አጥቂው አቡበከር ናስር እና አማካዩ ሽመልስ በቀለ ከቡድኑ ስብስብ ውጭ መሆናቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

አጥቂው አቡበከር ናስር ከህመሙ አገግሞ መጠነኛ ልምምድ ቢጀምርም ለቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ለመድረስ የሚያስችል የአካል ብቃት ደረጃ ላይ የማይገኝ በመሆኑ ከቡድኑ ስብስብ ውጭ መደረጉ ተገልጿል።

አማካዩ ሽመልስ በቀለ መቻል ከሀንበሪቾ ጋር ባደረገው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ የጡንቻ መሳሳብ ጉዳት በማስተናገዱ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ከዚህ ህመም ብዙ ባለማገገሙ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጭ ሆኗል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.