Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ አዲስ የ5 ዓመት የፋይናንስ አስተዳደር ሪፎርም ስትራቴጅክ ዕቅድ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ከ2016 እስከ 2020 ዓ.ም ባሉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ሪፎርም ስትራቴጅክ ዕቅድ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ አድርጓል፡፡

ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ውጤታማ የፋይናንስ አስተዳደር ያለውን ወሳኝ ጠቀሜታ በውል በመረዳትና ነባሩን ስትራቴጂ በጥልቀትና በስፋት በመገምገም ሚኒስቴሩ አዲሱን የሪፎርም ስትራቴጂ ዕቅድ ማዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

የፊሲካል ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ የስትራቴጂክ ዕቅዱ ይፋ መሆን የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደሩን ቀድሞ ከነበረበት ደረጃ የበለጠ በማሻሻል መንግስት ለዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማዳረስ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ ያመላክታል፡፡

አዲሱ የሪፎርም ስትራቴጅ ወደ መሬት ወርዶ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው በባለድርሻ አካላት መካከል በሚኖረው የጋራ ጥረትና መደጋገፍ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

ተጠያቂነትና ግልጽነት የሰፈነበት ውጤታማ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደርን በጋራ እውን ለማድረግ በትብብር መንፈስ መንቀሳቀስ ይገባናል ማለታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.