Fana: At a Speed of Life!

አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ‘የኛ ምርት’ የተሰኘ ኤግዚቢሽንና ባዛር በመጪው ታህሳስ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣2016፣ (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር ”ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ሃሳብ ከታህሳስ 3 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል።

አምራች ኢንተርፕራይዞች ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

አምራች ኢንተርፕራይዞችን ለማበረታታትም በርካታ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር መዘጋጀቱ ተመላክቷል።

መድረኩ ኢንተርፕራይዞች በምርት ትውውቅ፣ በገበያ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ልምድና መረጃ ልውውጥ እንዲያደርጉ ሚናው የጎላ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የሀገር በቀል አምራቾችን ቁጥር ለመጨመር፣ የነባሮችን የማምረት አቅም ለማሳደግ እና ተኪ ምርቶችን ለማበራከት ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል።

ከፊታችን ታህሳስ 3 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በስካይላይት ሆቴል ለሚካሄደው ኤግዚቢሽንና ባዛር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉም ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.