Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልጿል።
በቢሮው የትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ከላይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከመደበኛ ገቢ 10 ቢሊየን ብር ይሰበሰባል።
በተጨማሪም ቀሪው 2 ቢሊየን ብር ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰበሰብ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በሩብ ዓመቱ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡንም ተናግረዋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያሉ የገቢ አማራጮችን አሟጦ ለመሰብሰብ ከየካቲት እስከ የካቲት ንቅናቄ በማካሄድ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በሲሳይ ዱላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.