Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ከሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ከሱዳን የሽግግር መንግስት ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ በሱዳን የነበራቸውን የስራ ጊዜያቸውን ማጠናቀቃቸውን በማስመልከትም በሉአላዊ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አሸኛኘትም ተደርጎላቸዋል።

በሽኝቱ ወቅት በተደረገው ውይይትም ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን፥ የኢትዮጵያና የሱዳን ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱንና በተለያዩ ዘርፎች ለጋራ ጥቅም በትብብር መስራታቸውን ገልፀዋል።

በድንበር አከባቢም የሚያጋጥሙ ችግሮችንም በውይይት የመፍታት ልምዳቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ በሱዳን ቆይታቸው ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት መጠናከር ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነው በ2019 በሱዳን በነበረው የለውጥ እንቅስቃሴ ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ በለውጥ ሀይሎች እና በወታደራዊ የሽግግር ካውንስል መካከል የተካሄደው የድርድር ሂደት የተሳካ እንዲሆን ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

በተጨማሪም በሱዳን የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጫወቱትን ሚና በማውሳት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶም በበኩላቸው፥ በሱዳን በነበራቸው የስራ ቆይታ ወንድም በሆነው የሱዳን ህዝብና በተለያዩ የመንግስት ተቋማት አመራሮች ለስራቸው መሳካት ለተደረገላቸው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.