Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተማሪዎች ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የመጀመሪያው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የተማሪዎች የውድድር ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

በዚህ መሰረት ነገ ቅዳሜ ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም የአፍሪካ ተማሪዎች የሚወዳደሩበት ኤክስፖ ዝግጅት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሔድ ከአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

እሁድ ህዳር 2 ቀን 2016 ደግሞ የአፍሪካ ተማሪዎች የፍጻሜ ውድድር ዝግጅት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሔድ መሆኑን የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አስታውቋል።

በመድረኮቹ ላይም የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮችና ሚኒስትሮች እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.