Fana: At a Speed of Life!

በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚፈፀም ወንጀልን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕክምናና ተያያዥ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚፈፀም ወንጀልን ለመከላከያ የሚወጡ አሰራርና ደንቦች ተግባራዊ እንዲደረጉ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፍትሕ ሚኒስቴር “በህክምናና ተያያዥ የሙያ አገልግሎት አሰጣጥ የሚፈፀም ወንጀል የምርመራ እና ክስ ማኑዋል ” በሚል ስያሜ መስከረም 8 ቀን 2016 በጀት ዓመት አጽድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።

በዛሬው ዕለትም ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢ ከተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይትና የማኑዋሉን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡

በፍትሕሚኒስቴር የህግ ጥናት ማርቀቅ እና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አዲስ ጌትነት÷ ማኑዋሉ በህክምና ሙያ ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችን ለመመርመር ብሎም ክስ ለመመስረት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ማኑዋሉ ከመዘጋጀቱ በፊት የዳሰሳ ጥናቶች መደረጋቸውን የገለጹት ዳይሬክተር ጀነራሉ÷ ሌሎች ሀገራትም በዘርፉ ያላቸውን አሰራር መዳሰስ መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

በዳሰሳ ጥናቶቹም በዘርፉ የሚስተዋሉ ወንጀሎች መኖራቸውን ገልጸው÷ወንጀሉን ለማጣራትም ክፍተቶች ሲስተዋሉ እንደነበርም ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የማኑዋሉ ተግባራዊ መሆን በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ተናግረው÷ይህም የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በተጠናከረ መልኩ ለመመርመር እንደሚያገዝም አክለዋል፡፡

በተጨማሪም በህክምናው ዘርፍ ያለው ሙያዊ ስነ-ምግባር ከምንጊዜውም በላይ እንዲጠበቅ በማድረግ ባለሙያዎች ስራቸውን በነጻነት እንዲሰሩ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ማኑዋሉ ተግባራዊ ሆኖ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸው እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.