Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ቶትንሃም ተሸንፏል፡፡

በሜዳው በርንሌን ያስተናገደው አርሰናል ትሮሳርድ፣ ሳሊባ እና ዚንቼንኮ ባስቆጠሯቸው ግቦች 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ በኦልድ ትራፎርድ ሉተን ታዎንን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

የማንቼስተር ዩናይትድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ሊንደሎፍ ነው ያስቆጠረው ፡፡

በተመሳሰይ ክርስታል ፓላስ በሜዳው በኤቨርተን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

ቀደም ብሎ በተደረገ ጨዋታ ቶትንሃም ሆትስፐር ባልተጠበቀ ሁኔታ በዎልቭስ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.