Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዝየም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ አስትሮኖሚካል ኅብረት 386ኛ ሲምፖዝየም ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

“ጥቁር ሰማይና የሥነ-ፈለክ ቅርሶች አስትሮ ቱሪዝምን ለማሳደግ ያላቸው ሚና” በሚል መሪ ሐሳብ ነው ሲምፖዝየሙ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በሲምፖዝየሙ ላይ ከአፍሪካ፣ እስያና አውሮፓን ጨምሮ ከተለያዩ ክፍለ-ዓለማት የመጡ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የቀጣናዊ ትስስር መሪ ሥራ አስፈጻሚና የሲምፖዚየሙ ሰብሳቢ ዓለምዬ ማሞ እንዳሉት÷ ሲምፖዝየሙ በምሽት የሚታይ የተፈጥሮ የሰማይ ብርሃን ከሰው ሠራሽ ብርሃን የመጠበቅና የሥነ-ፈለክ ቅርሶች የተመለከቱ ምርምሮች የሚቀርቡበትና የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ነው።

የሥነ-ፈለክ ቱሪዝምን ለማሳደግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን እምቅ የጨለማ ሰማይ የቱሪዝም ሀብት ላይ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚካሄድም ነው የጠቆሙት፡፡

ከቱሪዝም ኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት ጋር በዘርፉ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግና የቱሪዝም ሀብቱን መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚካሄድም አመላክተዋል፡፡

እስከ ሕዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆው ሲምፖዝየሙ የተዘጋጀው÷ በዓለም አቀፉ አስትሮኖሚካል ኅብረት፣ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ትብብር መሆኑ ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.