Fana: At a Speed of Life!

የጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ልጆች ለአባታቸው ገዳዮች ይቅርታ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳዑዲው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ልጆች ለአባታቸው ገዳዮች ይቅርታ ማድረጋቸውን አስታወቁ።

የጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ወንድ ልጅ የሆነው ሳላህ ካሾጊ በትዊተር ገፁ ልጆቹ ለአባታቸው ገዳዮች ይቅርታ ማድረጋቸውን ይፋ አድርጓል።

በዚህ በተባረከው (የረመዳን ወር) የፈጣሪን ቃል ማሰብና ማስታወስ እንደሚያስፈልግ ያነሳው ሳላህ፥ አንድ ሰው ይቅር ካለ ዋጋው ከአላህ ነው ብሏል።

አያይዞም “እኛ የሰማዕት ጀማል ካሾጊ ልጆች የሃያሉን ፈጣሪ ሽልማት በመሻት አባታችንን የገደሉትን ይቅር ብለናቸዋል” ብሏል።

ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ በፈረንጆቹ 2018 ጥቅምት ወር ላይ በቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ የጋብቻ ማስረጃዎችን ለማግኘት በገባበት ወቅት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ይነገራል።

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2019 ደግሞ ከእርሱ ግድያ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ከዋሉ 11 ተጠርጣሪዎች መካከል 5 የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆን፥ ሶስቱ ደግሞ የ24 ዓመት እስር ቀሪዎቹ በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.