Fana: At a Speed of Life!

በዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ዓለም አቀፉን ፖለቲካዊ አሰላለፍ ማጤን እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በምታደርጋቸው ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች የዓለም አቀፉን የፖለቲካዊ አሰላለፍ ሂደት መሠረት ያደረገ ዝግጅት እንደሚያሥፈልጋት የዘርፉ ምሁራን አስገነዘቡ፡፡

ኢትዮጵያ ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በጥናት ላይ የተመሰረተ የጋራ ሐሳብ መያዝ እንደሚያስፈልጋት ምሁራኑ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያገለገሉት ተሻለ ሰብሮ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ አሁን የሚስተዋሉ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎችን በንቃት መከታተል ይገባል፡፡

እንደ ሀገር ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎችን ለማሳለፍም ሁለንተናዊ ዝግጅት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር በፍቃዱ ዳባ በበኩላቸው ÷ ኢትዮጵያ በተለይም የዓለምአቀፍ ተቋማት መቀመጫ መሆኗ ዓለምአቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ተፈላጊነቷን እንደሚያጎላው አንስተዋል፡፡

ይህንን ምቹ አጋጣሚም በኢንቨስትመንቱ እና በሌሎች መስኮች ለመጠቀም ተገቢውን ጥረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ባለፉት ወራት የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ፣ መሪዎችና ልዑኮች ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው÷ በፈተና ውስጥ ሆነንም ላስመዘገብናቸው ለውጦች ዓለምአቀፍ ተቋማት ጭምር የሰጡትን እውቅና መሰረት ያደረገ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.