Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉 በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ግጭትን በሚመለከት በየሰፈሩ በአማራም በኦሮሚያ ውስጥም ግጭቶች ይታያሉ፤ እነዚህ ግጭቶች ሰው የሚገሉ ንብረት የሚያወድሙ እንዲሁም ከጉዟችንን የሚያዘገዩ አላስፈላጊ ነገሮች ናቸው፤
👉 የእኛ መሻት ሁልጊዜም ሰላም ነው፤ የምንናገረው የምንተጋው፣ አብዝተን የምንሻው ሰላም በሀገራችን እንዲሰፍን ነው፣
👉 ኢትዮጵያን ሳታንስብንና ሳንቦጫጭቃት ብንጠግናት ብንሰራላት ብናበለጽጋት ግን ሀገራችን እንደ ስመጥር ሀገራት መሆን የሚያስችል ብቃት አላት፣
👉 ህዝብን ከሚያውክ ሀገርን ከሚያዳክም እርስ በእርስ ከሚያገዳድል ነገር መጠበቅ ያስፈልጋል፣
👉 አማራ እና ኦሮሞ በተደጋጋሚ እንዳነሳሁት ቢፈልጉም ባይፈልጉም በሰላም ለመኖር ያላቸው ምርጫ አንድ ብቻ ነው፤ ያንድ አባት ልጆችና የአንድ ሀገር ዜጎች እንዲሁም ወንድማማች መሆናቸውን አውቀው በተከባበረ አብሮ መኖር በሚያስችል ማንነት መጓዝ ብቻ ነው፣
👉 ታሪክ ሙያዊ ዘርፍ ነው፣ ሁሉም ሰው ታሪክን እኩል አይረዳውም፤ እኩል አይናገረውም፤ እኩል አይጽፈውም፤ በዘርፉ የተማሩ እንዴት ታሪክ እንደሚመረመር የሚያውቁ ሰዎች አሉ፣ሰዎች አሉ፡፡
👉 በአማራና በትግራይ ክልል መካከል ጥያቄ የሚነሳባቸው ቦታዎችን በሚመለከት ህግን የተከተለ፣ ዘላቂ ሰላምን ያከበረና የህዝብን አብሮነት ያስቀደመ የመፍትሄ አቅጣጫ እንከተል ብለን እየሰራን ነው፡፡
👉 ነገር ግን የእኛ ብቻ መፍትሄ ይተግበር አላልንም፡፡ ለዘላቂ ሰላምና ህዝቦች አብሮነት የሚሆን መፍትሄ ለሚያመጡ አካላትም በራችን ክፍት ነው፡፡
👉 የእኛ ፍላጎት በሁለቱም ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ ማየት ነው፡፡ የህዝቡም ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡
👉 የብሄራዊ መግባባት ጉዳይ ልናባክነው የማይገባ የሀገራችንን ሰላምሊያሰፍን የሚችል ትልቅ እድል ስለሆነ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡
👉 ኮሚሽኑ እንዲቋቋም በተለያዩ አካላት ሲጠየቅ የቆየ ነው ለተግባራዊነቱም በጋራ ልንሰራ ይገባል፡፡
👉 ብሄራዊ መግባባት በተለያዩ ዘርፎች እንደ ሀገር ያሉብንን ጥያቄዎች ለመመለስ አይነተኛ መንገድ ስለሆነ ብንጠቀምበት መልካም ነው፡፡
👉 ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የሚበጅ ስራ እንዲያከናውን ሁላችንም ልንደግፈው ይገባል፤ እድሉንም መጠቀም አለብን፡፡
👉 ይህ እድል ከባከነ መሰል እድሎችን ለማግኘት በርካታ ዓመታትን ሊፈጅብን ይችላል፡፡
👉 በ1953 ዓ.ም ለውጥን የመጠቀም እድል አግኝተን አምልጦናል፤ በ1966 እንዲሁም በ1983 ዓ.ም ድጋሚ እድል አግኝተን አልተጠቀምንበትም፡፡
👉 በመሆኑም አሁን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሚሰጠንን እድል በተገቢው መልኩ መጠቀም አለብን፡፡
በየሻምበል ምሕረትና አመለወርቅ ደምሰው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.