Fana: At a Speed of Life!

እስራዔል ከሃማስ ጋር እየተደራደረች መሆኑ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል ከሃማስ ጋር የታገቱባትን ንጹሐን ለማስለቀቅ እየተደራደረች መሆኑ ተገለጸ፡፡

አሁን ላይ ሁለቱ አካላት ጦርነቱን ማካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የያዟቸውን ንጹሃን ለመለዋወጥ መቃረባቸውም ነው የተገለጸው።

ድርድሩ ከተሳካ በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን የታገቱት በአብዛኛው ሴቶች እና ሕፃናት እንደሚለቀቁ አር ቲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ሃማስ እስከ 70 የሚደርሱ ሕጻናትን እና ሴቶችን ለመልቀቅ ዝግጁ እንደሆነም አስታውቋል።

በምላሹ እስራዔል የአምሥት ቀናት ተኩስ አቁም እንድትተገብር አንድ ሥማቸው ያልተጠቀሰ የሃማስ ጦር መሪ ጠይቀዋልም ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ቡድኑ እስረኞች እንዲለቀቁለት እና ዓለም አቀፋዊ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ ሳይጠይቅ አይቀርም እየተባለ ነው፡፡

እስራዔል በበኩሏ ከመስማማቷ በፊት ቡድኑ ስለሚለቃቸው ንጹሐን ዜጎቿ በቂ ማስረጃ እና ማረጋገጫ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.