Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በፈጠራ ስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ጃክ ማ ባዘጋጁት የፈጠራ ሥራ ባለቤቶች ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፈጠራ ስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ጃክ ማ ባዘጋጁት የፈጠራ ሥራ ባለቤቶች ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ቀደም ብሎ ከጃክ ማ ጋር ባደረጉት ውይይት ተጽዕኖ አሳዳሪ የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችን ለመደገፍ ታስቦ ስለ ተዘጋጀው የአፍሪካን የቢዝነስ ጀግኖች ( ww.africabusinessheroes.org/en/ ) መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በኮቪድ19 ወቅት የፈጠራ ሥራን ለመሥራት የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው፣ ብዙዎች ጠቃሚ ሐሳቦችን እያፈለቁ ይገኛሉም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በዚህም በፈጠራ ሥራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን በመሉ የድረ ገጹን መረጃ አንብበው በማመልከት በቀጠና ደረጃ የውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.