Fana: At a Speed of Life!

ዳስፖራው ለሀገራዊ ምክክሩ የበኩሉን ገንቢ ሚና እንዲጫወት ያለመ መድረክ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳስፖራው ማኅበረሰብ በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግና ለሀገራዊ ምክክሩ የበኩሉን ገንቢ ሚና እንዲጫወት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ መድረክ የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው፡፡

በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር የሚካሄደውን የውይይት መድረክን በተመለከተ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም÷ ዳያስፖራው በምክክር ሂደቱና ኮሚሽኑ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሮት በንቃት እንዲሳተፍና እንደ አንድ ባለድርሻ ተገቢውን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንዲችል መድረኩ ተዘጋጅቷል ብሏል፡፡

በተለያዩ ሀገራት የሚኖረው የዳያስፖራው ማኅበረሰብ የሚያበረክተውን በጎ ሚና ግምት ውስጥ በማስገባት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንዲካተትና እንዲሳተፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው መድረክም 700 ገደማ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

በመድረኩ ስለ ሀገራዊ ምክክር ምንነትና ዓላማዎች እንዲሁም ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራትና በቀጣይ ዕቅዶቹ ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ለሂደቱ መሳካት በዳያስፖራው ማኅበረሰብ ተሳትፎና ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.