Fana: At a Speed of Life!

በሕግ ቁጥጥር ስር ለነበሩ አካላት ሲሰጥ የቆየው የተሃድሶ ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሁከትና ግርግር ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ለነበሩ አካላት ሲሰጥ የቆየው የተሃድሶ ስልጠና ተጠናቋል።

የክልሉን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስና የሕዝቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ የተሃድሶ ሰልጣኞች ሕብረተሰቡን በማስተማር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ወንድወሰን ሁሴን ተናግረዋል።

የተሃድሶ ስልጠናው÷ በሰላም ምንነት፣ በሰላም አስፈላጊነት፣ ግጭትና ሁከት ሊያስከትሉ በሚችሉት አደጋዎች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኮማንድ ፖስቱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተጠርጣሪዎችን የሠላም ግንዛቤ በሚያሳድጉና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በሚያብራሩ ሐሳቦች ዙሪያም ስልጠና መሰጠቱንም ነው የተናገሩት።

ሰልጣኞችም ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ ስለ ሰላም ምንነትና ስለ ግጭት አስከፊነት እንዲሁም ከብጥብጥና ሁከት ይልቅ ሠላማዊ ውይይት አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን በማስረዳት የሚፈጠሩ ብዥታዎችን መቀየር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የተሃድሶ ሰልጣኞች በበኩላቸው÷ በክልሉ በተከሰተው ግጭት ሳቢያ የሰው ሕይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል በመሆኑም እንደዚህ አይነት ጥፋት ዳግም እንዳይከሰት የሰላምን ጠቀሜታ ለማኅበረሰቡ በማስገንዘብ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

በስልጠናው ጉዳያቸው ተጣርቶ ከወንጀል ድርጊት ነፃ የሆኑ፣ ከባድ ጉዳት ያላደረሱና ማስረጃ ያልቀረበባቸው 235 ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ከማረሚያ ቤቱ እንዲሰናበቱ ተደርጓል ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.