Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን ፍልሰት ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ ያለመ ፕሮጀክት 2ኛ ምዕራፍ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍልሰትን ለሴቶች ሕጋዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ ያለመ ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በተመድ ሴቶች ኤጀንሲ፣ በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት እና በጀርመን መንግስት በጋራ የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ሴቶች ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገራት፣ ከሌሎች ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ በኩል ዝውውር ሲያደርጉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ሕጋዊ እንዲሆኑ ማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ÷በሕገ ወጥ ፍልሰት ውስጥ ሴቶች ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ በመሆናቸው ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰት እንዲኖር ኢትዮጵያ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰት እንዲኖር ቅንጅታዊ አሰራር ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የተመድ ሴቶች ኤጀንሲ ሀገራዊ ተወካይ ወ/ሮ ሴሲሌ ሙካሩቡጋ በበኩላቸው÷ ሕጋዊ ፍልሰት እንዲኖር እና የሴቶችን ተጋላጭነት ለመቀነስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገራት በሚደረግ ፍልሰት ውስጥ 50 ከመቶዎቹ ሴቶች እንደሆኑ መናገራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.