Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ትብብር አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጻለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳር ይቬጀኒ ተርኺኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ባለው  የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ትብብር እንዲሁም  በመጪው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ ÷የሩሲያ መንግስት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያከናወነች ባለው ተስፋ ሰጪ የግብርና ስራ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ኢቭጄኒ ተርኺኒ በበከሉቸው÷ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን የሚኒስቴሩ  መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.