Fana: At a Speed of Life!

ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በሚደረገው የነዳጅ ዝውውር እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጂቡቲ ከሆሪዞን የነዳጅ ተርሚናል ጄኔራል ማናጀር ሁሴን አሕመድ ጋር በነዳጅ ዝውውር እንቅስቃሴ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የነዳጅ ዝውውር ለማቀላጠፍ በተርሚናሉ የሚሰጠውን የነዳጅ አቅርቦት ስርዓት እንዲሁም ከከባድ የጭነት አሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘ የሚሰጡ አገልግሎቶች የሚሻሻሉበት ሁኔታ ላይ ትኩረት በማድረግ መመከራቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ቀደም አምባሳደሩ የኢትዮጵያን የገቢ-ወጪ ዝውውር አስመልክቶ ከከባድ የመኪና አሽከርካሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው የጂቡቲ አካላት ጋር ውይይት እንደሚያርጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.