Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ችግኝ ማዘጋጀቱን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ማዘጋጀቱን ገለፀ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው እንግዳእየሁ እንደገለፁት፥ በክልሉ ለችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።

የቅድመ ዝግጅት ስራው ያለፈው አመት ችግኝ ተከላ እንደተጠናቀ መጀመሩንም ነው የተናገሩት።

በቅድመ ዝግጅት ስራው ባለፋት ሁለት አመታት የነበሩ ተግዳሮቶችና ስኬቶች ላይ ግምገማ በማድረግ ተግዳሮቶችን በመፍታት ስኬቶችን ለማስቀጠል ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል።

በዚህም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታና ከፍተኛ የመፅደቅ መጠን ያላቸውን ችግኞች ለመትከል እስካሁን 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ችግኝ ተቆጥሮ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

በበጀት አመቱ የክረምት ችግኝ ተከላ ወቅት 1 ነጥብ 75 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙን ያነሱት ዳይሬክተሩ፥ ለደንና ለጥምር ደን የችግኝ ተከላ የሚሆን 164 ሺህ ሄክታር መሬት ቦታ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

በችግኝ ተከላው ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍል የሚሳተፍ ሲሆን፥ የችግኝ ተከላው በሁለት ሜትር ርቀት የሚከናወን በመሆኑ ራስን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅና ለመከላከል አመች መሆኑን ጠቅሰዋል።

ባለፈው አመት ከተተከለው ችግኝ ውስጥ 84 በመቶ የሚሆነው መፅደቁን ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.