Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 441ኛው ኢድ አል ፈጥር እሁድ ይከበራል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት ጨረቃ ባለመታየቷ 1 ሺህ 441ኛው ኢድ አል ፈጥር እሁድ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ኡስማን አደም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁትም በዓሉ ከነገ በስቲያ ማለትም እሁድ ይከበራል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ 1 ሺህ 441ኛውን ኢድ አል ፈጥር በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ህዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን የኢድ በዓል ሲያከብር የኮሮና ቫይረስ የተከሰተበት ወቅት በመሆኑ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።

በመሆኑም ሁሉም የኢድ ሰላትን በየቤታቸው ሆነው እንዲሰግዱ አሳስበዋል።

በዓሉ ሲከበርም የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን እንዲሁም አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንደሚገባውም ተናግረዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.