Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው የትምህርት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር የመስራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የትምህርት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከድርጅቱ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ጃሰን ጂን(ዶ/ር) ጋር መክረዋል፡፡

በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ላይ እያከናወናቸው ስላለው ተግባራት እና ሀገራዊ የልማት አቅጣጫዎችን አስረድተዋል፡፡

የቤጂንግ ዌዋ የመስመር ላይ የትምህርት ቴክኖሎጂ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ጃሰን ጂን(ዶ/ር)፥ ድርጅታቸው ለትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሥራውን የሚያቀሉ ዲጂታል የትምህርት ቴክኖሎጂዎችን እንደሚያቀርብና በክህሎት ልማቱ ዘርፍ ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ መሆኑን የጠቆሙት ጃሰን ጂን(ዶ/ር) በቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና መሰል የሥልጠና ዘርፎች ዘመኑን የዋጁ “ሲሙሌተሮችን” በመጠቀም ደረጃውንና ጥራቱን የጠበቀ ሥልጠና መስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

ድርጅቱ በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎት አድንቀው ይህም ከክህሎት ልማቱ ባለፈ የሁለቱን ሀገራት የረዥም ጊዜ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.