Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባዔ አገኘሁ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከርና ሁለንተናዊ ትብብሩን ማሳደግ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

አፈ ጉባዔው ለቻይና ብሔራዊ ሕዝብ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ሎሳንግ ጊልትሰንና ልዑካን ቡድናቸውን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ተገኝተው ሽኝት አድርገዋል፡፡

በዚሁ ወቅት አፈ ጉባዔ አገኘሁ÷ በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከርና ሁለንተናዊ ትብብሩን ማሳደግ ላይ በትኩረት የሚሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ላደረገው ይፋዊ የስራ ጉብኝትም ምስጋና ማቅረባቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የቻይና ብሔራዊ ሕዝብ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ሎሳንግ ጊልትሰ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ መደሰታቸውን በመግለጽ፤ አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በቻይና የስራ ጉብኝት እንዲያርጉ ጋብዘዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.