Fana: At a Speed of Life!

በ3ኛ ዙር እየሰለጠኑ የሚገኙ አመራሮች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል ርዕስ በተለያዩ አካባቢዎች በ3ኛ ዙር እየሰለጠኑ የሚገኙ የመንግስት አመራሮች እየተሰሩ የሚገኙ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ በ3ኛ ዙር እየሰለጠኑ የሚገኙ የመንግስት አመራሮች በመዲና እየተሰሩ የሚገኙ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በአምስቱም የከተማዋ በር እየተገነቡ ከሚገኙ ግዙፍ የገበያ ማዕከላት ውስጥ አንዱ የሆነውን የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች መሸጫ የግብርና ማዕከልን ተመልክተዋል፡፡

በዚህም መሰል የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነቱን በእጅጉ እንደሚያቃልሉ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መግለጻቸውን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

የገበያ ማዕከሉ አምራቹን እና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ በቴክኖሎጂ የዘመኑ የጅምላና የችርቻሮ መሸጫ ሱቆች ያሉት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሐረሪ ክልሎች በሚገኙ ማዕከላት ስልጠና የሚከታተሉ የመንግስት አመራር አባላት በየአካባቢው የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በባህርዳር እና ጎንደር ከተሞች የስልጠና ማእከል እየተሳተፉ የሚገኙ አራሮችም ከስልጠናው ጎን ለጎን በከተማዎቹ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱ በአመራሩ ዘንድ የልምድ ልውውጥ በማከናወን ልማትን ለማፋጠንና በየአካባቢው ተመሳሳይ ልማትን ለማምጣት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.