Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአህጉሪቱን የመሬት ፖሊሲ አቅም ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ጉባኤውን የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ማዕከል፣ የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት በተባባሪነት እንዳዘጋጁት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል።

ጉባኤው “ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሥምምነት ትግበራ” በሚል መሪ ቃል በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እንደሚካሄድም በመረጃው ተጠቅሷል።

የጉባኤው ዋና አላማም የአፍሪካ ሀገራትን የመሬት ፖሊሲ ትግበራን በመረጃ፣ ክህሎትና እውቀት ማሳደግ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ መወያየት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የአህጉሪቱን የመሬት ፖሊሲ አቅም ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጉባኤው ከነገ ጀምሮ እስከ ፊታችን አርብ ድረስ የሚካሄድ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.