Fana: At a Speed of Life!

ተሞክሮዎችን በመቀያየር የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ለውጤት ያበቃሉ – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን እየለማ ያለው የሩዝ ሰብል ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም ባደረጉት ንግግር÷ ልምዶችን በመቀያየር የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ለውጤት እንደሚያበቁ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በጅማ ከተማ ውስጥ እየተሠሩ የሚገኙ የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን መጎብኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

እንዲህ ዓይነት ልማቶች ከዘርፉ የገቢ ምንጭ ማግኘት እንደሚቻል ማሣያ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በሌሎች ከተሞች የሚገኙ ወንዞችንም በዚህ አግባብ በማልማት የገቢ ማግኛ ለማድረግ እንሠራለን ሲሉም አመላክተዋል፡፡

በየአካባቢው ያሉትን የተሻሉ ተሞክሮዎችን በመቀያየር የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ለውጤት እንደሚያበቁም አቶ አረጋ ከበደ አስገንዝበዋል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.