Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የ3 ሺህ 757 የላብራቶሪ ምርመራ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 15 እስከ 70 እድሜ ክልል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 48 ከአዲስ አበባ ፣ 3 ሰዎች ከአፋር ፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል ፣ 7 ሰዎች ከሶማሌ ክልል እና 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 11 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ 5 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንኪኪ ያላቸው ሲሆን 45 ሰዎች ግን ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 23 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151 ደርሷል።

ኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ 76 ሺህ 962 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ችላለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.