Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ካቢኔ የታክስ ጫና ማቃለያ እና ውዝፍ እዳ ስረዛ እንዲደረግ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፎአል፡፡

በዚህም ከ1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆንላቸው ውስኗል።

ካቢኔው ከ2008 – 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር ብቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፎል፡፡

በሌላ በኩል የከተማዋን ገቢ ለማሻሻል ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያላቸውን አቅም በዝርዝር ፈተሸው ለከተማዋ ገቢ እድገት በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ዙሪያና አፈፃፀሙንም የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መንገድ ላይ መወያየቱን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የታክስ መሰረትን በማስፋት በተለይም ማዘጋጃቤታዊ እና የከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅምና አሰራር በተሻለ መልክ በማደራጀት የ2013 ዓም በጀት በመካከለኛ ገቢ ምጣኔ መሰረት ተዘጋጅቶ ለውይይት እንዲቀርብ ተወስኗል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.