Fana: At a Speed of Life!

ለ7 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ የማድረስ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ7 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ የማድረስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡
 
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ በራስ አቅም ለተረጂዎች ድጋፍ የማቅረብ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው አመላክተዋል።
 
ድጋፉ በአየር ንብረት ለውጥ እና በጎርፍ ምክንያት ለእርዳታ ጠባቂነት ለተዳረጉ ዜጎች የሚዳረስ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
 
አማራ ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች ላይ ያሉ አካባቢዎች በድርቅ ሲመቱ፥ ሰባት ክልሎች ላይ ደግሞ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል ያሉት ኮሚሽነሩ በዚህም 7 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች ለእርዳታ ጠባቂነት ተዳርገዋል ብለዋል።
 
ከእነዚህም ውስጥ 4 ሚሊየን ያህሉ የተፈናቀሉ መሆናቸው በመግለጫው ተመላክቷል።
 
52 በመቶ እርዳታ ፈላጊዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሲሆን 48 በመቶዎቹ ደግሞ መንግስት በራሱ መንገድ እያገዛቸው ያሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
 
እስካሁንም የምግብ፣ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ በሁለት ዙር ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።
 
እስካለፈው ሳምንት ድረስ አጋር አካላት ድጋፋቸውን በማቆማቸው ሁሉም ተረጂዎች ሙሉ በሙሉ በመንግስት ድጋፍ እየተደረገላቸው መቆየታቸውንም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
 
ይሁን እንጂ በአማራ ክልል በተለይም በሰሜን ጎንደር ፣ በደቡብ ጎንደር ጋይንት እና ዋግ ኸምራ ባለው የጸጥታ ሁኔታ እርዳታ ለማድረስ ፈታኝ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
 
በትእግስት አብርሃም
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.