Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስ ሙዚዬም አፍሪካን በሳይንስ ዘርፍ ወደ ፊት ለማሻገር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚዬም አፍሪካን በሳይንስ ዘርፍ ወደፊት ለማሻገር አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት የፓን አፍሪካ ፓርላማ አባላት ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ የጋራ ስብሰባቸውን እያካሄዱ የሚገኙት የፓን አፍሪካ ፓርላማ አባላትና ቋሚ ኮሚቴዎች የሳይንስ ሙዚዬምን እና አንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡

አባላቱ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ እያደረጋቸው ያሉ የልማት ስራዎች በአፍሪካ አርአያ የሚሆኑ ናቸው፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ በስፋት ሊሰሩ እንደሚገባ በመጥቀስም፥ እንደ ሳይንስ ሙዚዬም ዓይነት መሰረተ ልማቶች ለአፍሪካ እድገት ወሳኝ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

የፓን አፍሪካ ፓርላማ አባላትና ቋሚ ኮሚቴዎች የጋራ ስብሰባ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕጋዊ ያልሆነ የመንግስት ምስረታ እና የፓርላማ ዲፕሎማሲ ላይ እየመከረ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.