Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት የምግብ ቅቤ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት የምግብ ቅቤ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የምግብ ቅቤው የተያዘው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መሆኑ ተገልጿል።

የአለም ባንክ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል መከላከል ሽፍት ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ገብሬ ድንበሩ እንደገለጹት÷ ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ በመከተል ባደረገው ክትትል የተበላሸና የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን 3 ካርቶን የምግብ ቅቤ ይዟል።

በጉዳዩ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦችም አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

ማህበረሰቡ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምርቶች በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት በመገንዘብ መሰል ድርጊቶችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.