Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ልዩነቶችን ለማጥበብ እየተከናወነ ያለው ሥራ አበረታች ነው ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዲጂታል ልዩነቶችን ለማጥበብ እያከናወነች ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን እና የአይ ሲ ቲ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ 5ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ÷ የኢትዮጵያ ተወካዮች የዲጂታል ዕድገት ልዩነቶችን ለማጥበብ ከሕግ ማዕቀፍ፣ ከዐቅም ግንባታ፣ ከበይነ-መረብ (ኢንተርኔት) ተደራሽነት፣ ከማበረታቻና ድጋፍ ተግባራት አኳያ ያከናወኗቸውን ተግባራት አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከ400 በላይ አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ተደራሽ ማድረጓ የተገለጸ ሲሆን÷ ይህም በጥሩ ተሞክሮነት እንደሚወሰድ ተነስቷል፡፡

ኢትዮጵያ በኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች ልማት እና በበይነ-መረብ ተደራሽነት ረገድ እያከናወነች ያለው ተግባር በመድረኩ ተሳታፊዎች ተደንቋል፡፡

የኢትዮጵያን ተሞክሮም ተሳታፊ ሀገራት ሊጋሩት እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

በቴክኒክ ኮሚቴው ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨምሮ 35 የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት እየተሳተፉ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.