Fana: At a Speed of Life!

ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የሕዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ከድልማግስት ኢብራሂም እንደገለጹት÷ በክልሎችም የትራንስፖርት ስምሪት ክፍተት እንዳይኖር በጋራ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ከ187 በላይ ተደራሽ በሆኑ ሀገር አቆራጭ መስመሮች ተማሪዎቹን ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለማድረስ ዝግጅት መጠናቀቁንም ነው ያመላከቱት፡፡

ተማሪዎቹ አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉት በመናኸሪያ ብቻ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ከታሪፍ በላይ ገንዘብ እንዳይከፍሉና በትርፍ እንዳይጫኑም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ ችግር ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 9719 ላይ በመደወል ማሳወቅ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.