Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ በመላው ሃገሪቱ 1 ሺህ 441ኛው ኢድ አልፈጥር በአል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በመላው ሃገሪቱ 1 ሺህ 441ኛው የኢድ አልፈጥር በአል ተከበረ።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የረመዳንን ጾም መገባደድ ተከትሎ የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በአል በመላው የሃገሪቱ በተለያየ መልኩ ተከብሮ ውሏል።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ታላቁ የረመዳን ወር ያለፈበት ወቅት ለወትሮው በጾም ወቅት ይፈጸሙ የነበሩ ተግባራትን እንደከዚቀደሙ እንዳይፈጸሙ ያደረገ ነበር ብለዋል፡፡

ሆኖም ሁኔታው የፈጠረውን ጫና ለመቋቋም ያስችል ዘንድ ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወራት ህዝበ ሙስሊሙ አሰተምሮዎችን በመገናኛ ብዙሃን ማግኘት በመቻሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው እንዳነሱት በአሉ ሲከበር በሃይማኖታዊ አስተምህሮ መሰረት ያለው ለሌለው በማካፈል መሆን እንዳለበትም ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.