Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መመስረት ህዝቡን ተጠቃሚ በማድረግ ሊገለጽ ይገባል – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መመስረት ህዝቡን ተጠቃሚ በማድረግ ሊገለጽ ይገባል ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ እና የምስጋና መርሐ-ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ብሄር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የዋሉ ያደሩ ጥያቄዎችን በመመለስ ትልቅ ድርሻ እየተወጣ ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ሲጠየቁ የነበሩ የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ብልጽግና ፓርቲና የሀገራዊ ለውጡ አመራር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ መቆየቱን ተናግረዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ አዳዲስ ሦስት ክልሎች መመስረታቸውን ገልጸው፥ ከተመሰረቱት ክልሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ከተመዘገቡ 76 ብሄር ብሔረሰቦች 32ቱ ብሄር ብሔረሰቦች የሚኖሩበት እንደሆነም ነው ያነሱት፡፡

የክልሉ ምስረታ ወደ መሬት ወርዶ ህዝብን ተጠቃሚ በማድረግ ሊገለጽ እንደሚገባ ገልጸው፥ ይሕም የክልሉ አመራር ድርሻ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አክለውም፥ የሕዝቡ የልማት፣ የሥራ እድልና ሌሎችን ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግም ነው የገለጹት፡፡

በመጀመሪያም ይህን ጥያቄ ያነሳው ህብረተሰብ በአግባቡ መልስ እንዲሰጠው ለክልሉ አመራር አደራ ያሉ ሲሆን ፥ የክልሉ ህዝብም አመራሩ ስራውን እንዲሰራ ጊዜ በመስጠት ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል፡፡

የክልል መንግስታት፣ ባለሃብቶችና ህብረተሰቡ ክልሉ አዲስ በመሆኑ ለማጠናከሪያና ለመቋቋሚያ ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.